Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የሰፈነውን ሰላም ጠብቆ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተገኘውን ሰላም ጠብቆ ማስቀጠል እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር እና የሰላምና የፀጥታ ካቢኔ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ታደሰ ወረደ አስገነዘቡ፡፡

ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ ሐሳብ የዓለም የሰላም ቀን በመቐለ ከተማ ተከብሯል።

ቀኑን አስመልክቶ በተካሄደ መድረክ ላይ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ ባደረጉት ንግግር÷ የተገኘውን ሰላም ጠብቆና ተንከባክቦ ለዘላቂነቱ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

በየደረጃው ያለው አመራርም ይህን ተገንዝቦ መሥራት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት÷ በክልሉ የሰፈነውን ሰላም በማፅናት ልማትና የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማስቀጠል ከጊዜያዊ አሥተዳደሩ ጎን ሆነን እንሠራለን ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.