Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም በተጀመረው የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ አርባምንጭ ከተማን አሸንፏል።

ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ቻርልስ ሙሰጌ እና መሐመድኑር ናስር ባስቆጠሯቸው ግቦች አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

አርባምንጭ ከተማን ከሽንፈት ያላዳነውን ብቸኛ ግብ አህመድ ሁሴን አስቆጥሯል።

ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው የሊጉ መክፈቻ ጨዋታ ሃድያ ሆሳዕና መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.