ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ግንኙነትይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጻለች፡፡
በኩባ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አየለ ሊሬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳልቫዶር አንቶኒዮ ቫልዴስ ሜሳ አቅርበዋል።
አምባሳደር አየለ ከፕሬዚዳንትሣህለወርቅ ዘውዴ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከ የመልካም ምኞት መልዕክት ለኩባ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አስተላልፈዋል።
ም/ፕሬዚዳንት ሳልቫዶር አንቶኒዮ ቫልዴስ ሜሳ÷ ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን መድረኮች ለኩባ ላደረገችው የማያወላውል ድጋፍ ማመስገናቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡
አምባሳደር አየለ በበኩላቸው÷በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በማስታወስ አሁን ላይ ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡