Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቹን ቁጥር 83 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ በተያዘው በጀት ዓመት የደንበኞቹን ቁጥር 83 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን ገለጸ።

የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ኢትዮ ቴሌኮምን የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በሚመለከት በሰጡት መግለጫ፤ ኩባንያው በተያዘው አመት 163 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ተናግረዋል፡፡

በበጀት አመቱ የደንበኞቹን ቁጥር 83 ሚሊየን ለማድረስ እንዲሁም የቴሌብር ደንበኞቹን 55 ሚሊየን ለማድረስም ማቀዱንም ገልጸዋል።

በዚህ አመት 1 ሺህ ቀበሌዎች የቴሌኮም አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚደረግም ጠቅሰው፤ ከ1 ሺህ 200 በላይ አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች በዚህ አመት እንደሚገነቡ ጠቁመዋል።

የዲጅታል ኢትዮጵያና ዲጂታል ኢኮኖሚ አስተማማኝና በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆንም እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.