Fana: At a Speed of Life!

የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ ዝግጅት እየተደረገ ነው – ፌዴራል ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ እና ደኅንነት አካላት ጋር ሀገራዊ የጸጥታ ሁኔታዎችን ገምግሟል።

በግምገማው በጳጉሜን ቀናት የተካሄዱ ፕሮግራሞች፣ የ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫና የመውሊድ በዓላት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለምንም የጸጥታ ችግር መከበራቸው ተገልጿል፡፡

ወደ አዲስ አበባ ከተማና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ሰርገው ለመግባት ሲሞክሩ የነበሩ የሸኔ እና የጽንፈኛው ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በመዲናዋ ሞባይል ንጥቂያና ተደራጅተው የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ሕብረተሰቡን የሚያውኩ ቡድኖችና ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራው እየተደረገባቸው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በተከናወኑ የወንጀል መከላክል ተግባራት የአዲስ አበባ የጸጥታ ሁኔታ አሁን ላይ በአስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት ላይ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

በቀጣይም በአደባባይ በከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር የሚከበሩት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ ከወዲሁ ጠንካራ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተነስቷል፡፡

ለበዓለቱ በርካታ የጸጥታ ሃይል እንደሚሰማራና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ መጠቀሱን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.