Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት መለኪያ ደረጃዋን አሻሻለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት መለኪያ ደረጃዋን አሻሻለች፡፡

በየሁለት ዓመቱ የሚወጣው የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፋዊ የኢ-መንግሥት መለኪያ ትናንት በኒዮርክ  ከመንግሥታቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ይፋ ሆኗል።

ይህ ዓለም አቀፋዊ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት መለኪያ የዓለም ሀገራት በየሁለት ዓመቱ ከሌሎች ሀገራት አንጻር እና በራሳቸው ካሳዩት እድገት ጋር በማነጻጸር ሀገራቱ በዘርፉ ያደረጉትን መሻሻሎች ብሎም ያስመዘገቧቸውን ለውጦች የሚያሳይ ነው።

በዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት ሪፖርት መሠረት ኢትዮጵያ ከነበረችበት 10 ደረጃዎችን ማሻሻል ችላለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.