Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ “ኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር 2017” ዐውደ-ርዕይ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር 2017” የተሰኘ ዐውደ-ርዕይ ከመስከረም 18 እስከ 24 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊካሄድ ነው፡፡

በዐውደ-ርዕዩ ላይ የፓናል ውይይቶችን ጨምሮ፣ የባሕል ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና የሙዚቃ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡

ኢሬቻ የአብሮነት ምልክት መሆኑን እና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶቹን ለማስተዋወቅ ዐውደ-ርዕዩ እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

በዐውደ-ርዕዩ ከ250 ሺህ በላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቅሷል፡፡

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.