Fana: At a Speed of Life!

ብራዚላዊው ታዳጊ ኤንድሪክ በሪያል ማድሪድ መለያ በዕድሜ ትንሹ የቻምፒዮንስ ሊግ ግብ አስቆጣሪ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ታዳጊ ኤንድሪክ ትናንት ምሽት ስቱትጋርት ላይ ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ በሪያል ማድሪድ ታሪክ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በትንሽ ዕድሜ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰን ባለቤት ሆኗል፡፡

ኤንድሪክ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የብራዚሉን ክለብ ፓልሜራስን በመልቀቅ ነጭ ለባሾቹን (ማሬንጌዎቹን) መቀላቀሉ ይታወቃል፡፡

ትናንት ሪያል ማድሪድ የጀርመኑ ስቱትጋርትን 3 ለ 1 በአሸነፈበት ጨዋታም ኤንድሪክ በ95ኛው ደቂቃ ለክለቡ ግብ አስቆጥሯል፡፡

ይህን ተከትሎም ለሪያል ማድሪድ በ18 ዓመት ከ58 ቀን ግብ ያስቆጠረ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡

በክለቡ የሪከርዱ ባለቤት የነበረው ራውል ጎንዛሌዝ በፈረንጆቹ 1995 ክለቡ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከሀንጋሪው ፈረንክቫሮስ ጋር ሲጫወት በ18 ዓመት ከ113 ቀናት በዕድሜ ትንሹ ግብ አስቆጣሪ እንደነበር ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.