Fana: At a Speed of Life!

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ለሀገራችን ዴሞክራሲን በመሻት ታግለዋል- ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ለሀገራችን ዴሞክራሲን በመሻት ከታገሉት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ናቸው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ሕልፈተ-ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

በአስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክትም÷ በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ዜና እረፍት የተሰማኝን ሐዘን እገልጻለሁ ብለዋል፡፡

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ለሀገራችን ዴሞክራሲን በመሻት ከታገሉት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ናቸው ማለታቸውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ሠላማዊ ትግልን፣ የሐሳብ የበላይነትን፣ ሐሳብን መሞገትን ጨምሮ በርካታ ሀገራዊ ጠቃሚ ጉዳዮችን የፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅት ለማንጸባረቅ ጥረት ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል፡፡

ለቤተሰባቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.