በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ሰላማዊ መንገድን መርጠው በጽናት የታገሉ ናቸው – ኢሶዴፓ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ሰላማዊ መንገድን መርጠው በጽናት የታገሉ ናቸው ሲል ፓርቲያቸው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ገለጸ።
የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ራሔል ባፌ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፤ በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ለኢትዮጵያ የዕድሜ ልክ ዋጋ ከፍለው ያለ ዕረፍት ያረፉ ናቸው ብለዋል።
በዚህም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ሰላማዊ መንገድን መርጠው በፅናት በመታገል ዋጋ መክፈላቸውን ገልጸዋል።
በፖለቲካ መድረክ በሰላማዊ ትግል የሚታወቁት ታሪክ አዋቂው በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በህይወት ዘመናቸው የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ተናግረዋል።
በፖለቲካ እንቅስቃሴ ሰላማዊ መንገድ አማራጭ የሌለው ስለመሆኑ እምነታቸው እንደነበረ አስታውሰው፤ በዚህ እሳቤያቸውም ያለ ዕረፍት ለኢትዮጵያ ዋጋ ከፍለው ያለፉ ናቸውም ሲሉ አስረድተዋል።
ራሔል ባፌ (ዶ/ር) በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ህልፈተ ህይወት የተሰማቸው ሐዘንም በፓርቲው ስም ገልፀዋል፡፡
በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር)÷ የኢሶዴፓ ሊቀ-መንበር ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡
በሰለሞን ይታየው