Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ፑቲን የሩሲያ ወታደሮች ቁጥር በ180 ሺህ እንዲጨምር አዘዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገሪቱ ወታደሮች ቁጥር በ180 ሺህ እንዲጨምር ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

ፕሬዚዳንረቱ የሩሲያ ወታደሮችን ቁጥር መጨመር የሚያስችል አዋጅ መፈረማቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህን ተከትሎም የሩሲያ ወታደሮች አጠቃላይ ቁጥር 2 ነጥብ 4 ሚሊየን እንደሚጠጋ ነው የተመላከተው፡፡

አዋጁ ጠንካራ እና የማይደፈር የሩሲያ ሰራዊት ለመገንባት ያለመ መሆኑን የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ተናግረው፤ እርምጃው በሩሲያ ላይ የሚካሄዱትን የእጅ አዙር ጦርነት ለመመከት እንደሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን መንግስት ለሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስፈላጊውን በጀት እንዲመድብ ትዕዛዝ መስጠታቸውንም አርቲ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባች ወዲህ ፑቲን የሀገራቸው ወታደሮች ቁጥር እንዲጨምር ትዕዛዝ ሲሰጡ የአሁኑ ለ3ኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.