Fana: At a Speed of Life!

ለዓለም ዓቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ እጩዎች ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓለም ዓቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ሰባት እጩዎች ተለይተው ታወቁ።

የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት እንግሊዛዊው ሎርድ ሰባስቲያን ኮ ከእጩ ተወዳዳሪዎቹ መካከል እንደሚገኙበት ተነግሯል።

በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር በሎስአንጀለስና ሞስኮ ኦሊምፒክ ባለ ድል የነበሩት ሰባስቲያን ኮ በአሁኑ ወቅት የኦሎምፒክ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት የሆኑትን ቶማስ ባችን ለመተካት ከሚወዳደሩ ሰባት እጩዎች ጋር ይፎካከራሉ።

የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባች በሁለት ዙር ተቋሙን ከመሩ በኋላ በቅርቡ በፓሪስ በተካሄደው 33ኛው ኦሊምፒክ ላይ ሃላፊነታቸውን እንደሚለቁ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

በዚህም የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ለመሆን ሰባስቲያን ኮ እንዲሁም ስፔናዊው ሁዋን አንቶኒዮ ጁኒየር፣ ፈረንሳዊው ዴቪድ ላፓረቲየንት፣ ዚምባቡያዊቷ ክሪስቲ ኮቨንተሪይ፣ ጃፓናዊው ሞሪናሪ ዋታናቤ፣ ስዊዲናዊው ጆሃን አሊያስች እና የጆርዳኑ ልኡል ፋይሰል አል ሁሴን ለመወዳደር እጩ ሆነው እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

የሰባት ጊዜ የኦሊምፒክ የዉሃ ዋና ቻምፒዮናዋ ክሪስቲ ኮቨንተሪይ የመጀመሪዋ ሴት እንዲሁም አፍሪካዊት ፕሬዚዳንት ለመሆን ትወዳደራለች።

የህግ ባለሙያው ጀርመናዊው ቶማስ ባች ከፈርንጆቹ 2013 ጀምሮ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገሉ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.