የጃክሰን 5 መስራቹ ቲቶ ጃክሰን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂውን የፖፕ ሙዚቃ ንጉስ ማይክል ጃክሰንን ጨምሮ አምስት አባላት ያሉትን ‘የጃክሰን 5’ የሙዚቀኞች ቡድን የመሰረተው ቲቶ ጃክሰን በ70 አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
ቲቶ ጃክሰን ለህልፈተ ህይወት የተዳረገው በልብ ህመም ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።
በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ ‘ጃክሰን 5’ በሚል ከእህቱ ማይክልን ጃክሰንን ጨምሮ ከወንድሞቹ ጋር ባቋቋመው የጃክሰን 5 የሙዚቃ ባንድ ለዓለም ኪነ ጥበብ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከተው ቲቶ ጃክሰን ባደረበት የልብ ህምም ትናንት ማለፉ ተነግሯል።
ዳንሰኛ፣ አቀንቃኝ እና ጊታር ተጫዋች የነበረው ቲቶ ጃክሰን ከባንዱ ጋር በመሆን ሼክ ዩር ቦዲ፣ ዳውን ቱ ዘ ግራውንድ እና ኢንጆይ ዩርሰልፍ በሚል ያቀነቀኗቸው ሙዚቃዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አድማጭ በማግኘት በቢልቦረድ ሰንጠርዥ ምርጥ 10 ውስጥ መካተት የቻሉ ነበሩ።
በአሜሪካ የሙዚቃ ታሪክ ከፍተኛ ቦታ እንዳለው የሚነገርለት ቲቶ ጃክሰን ሶሎ፣ አር ኤንድ ቢ ጨምሮ ሌሎች የሙዚቃ ስልቶችን በመጫወት ይታወቃል፡፡
ቲቶ ጃክስን በብሪታኒያ የዝነኞች የሙዚቃ ውድድር ላይ ዳኛ እንዲሁም የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ በመሆን ማገልገሉም ይታወቃል።