Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡

ትምህርቱ  በመዲናዋ በሚገኙ በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ነው የተጀመረው፡፡

የመማር ማስተማር ሒደቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር አስጀምረዋል።

ተማሪዎች ለትምህርት አገልግሎት ከሚጠቀሙባቸው የመማሪያ ቁሳቁስ ባሻገር የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ ሌሎች የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው መምጣት እንደማይችሉ  መገለጹን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.