የመውሊድ በዓል በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በሐረር፣ በጎንደር፣ በጅማ ከተሞች እየተከበረ ነው፡፡
የመውሊድ በዓል የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) መልካም ተግባራትን የህይወት መርሕ ለማድረግ በማሰብ የሚከበር በዓል ነው።
በሐረር ከተማ ሸዋበር በተባው ስፍራ የሐይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮችና የተለያዩ አካላት በተገኙበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡
በተመሳሳይ በዓሉ በጅማ ከተማ መድረሰቱል ኸይርያ ቅጥር ጊቢ እየተከበረ ይገኛል።
የጅማ ከተማ ሙኒር መስጂድ ኢማም ሼህ መሀመድ አባ ተማም በስነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በዓሉ ያለው ለሌለው አካፍሎ ሁሉም በጋራ የሚያከብረው ስለሆነ የነብዩን ሱና በተከተለ መልኩና መረዳዳት በተሞላበት መንፈስ ሊከበር ይገባል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም 1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በጎንደር ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው።
በአብዱረህማን መሀመድ እና በተሾመ ሀይሉ