Fana: At a Speed of Life!

ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሲቀጥል ቶተንሃም አርሰናልን ያስተናግዳል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በሰሜን ለንደን ደርቢ ቶተንሃም ሆትስፐር አርሰናልን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

12 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ዎልቭስ ኒውካስል ዩናይትድን ያስተናግዳል።

ትናንት በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ሳውዝአምፕተንን 3 ለ 0፣ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ብሬንትፎርድን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል።

አስቶንቪላ ኤቨርተንን 3 ለ 2 እንዲሁም ከሜዳው ውጪ የተጫወተው ቼልሲ ቦርንማውዝን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

ሊቨርፑል በሜዳው በኖቲንግሃም ፎረስት 1 ለ 0 ሲሸነፍ፤ ብራይተንና ኢፕስዊች ታውን 0 ለ 0፣ ክርስታል ፓላስና ሌስተር ሲቲ 2 ለ 2 እንዲሁም ፉልሃምና ዌስትሃም ዩናይትድ 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.