Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼስተር ሲቲ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ሽንፈት አስተናግዷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስቴዲየም ብሬንትፎርድን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የማንቺስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኧርሊግ ሃላንድ ሲያስቆጥር የንቦቹን ብቸኛ ግብ ደግሞ ዮዋኔ ዊሳ አስቆጥሯል፡፡

ኧርሊንግ ሃላንድ በፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በመጀመሪያዎቹ 4 የሊጉ ጨዋታዎች 9 ግቦችን በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጫዋች መሆን ችሏል።

ሊቨርፑል ከተከታታይ ድሉ በኋላ በሜዳው ና በደጋፊው ፊት በኖቲንግሃም ፎረስት 1 ለ 0 ሲሸነፍ የቀድሞ የቼልሲ ተጫዋች ሁድሰን ኦዶዬ ግቧን ከመረብ አሳርፏል፡፡

በተመሳሳይ 11 ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ብራይተንና ኢፕስዊች ታውን 0 ለ 0 ፣ ክርስታል ፓላስና ሌስተር ሲቲ 2 ለ 2 እንዲሁም ፉልሃምና ዌስትሃም ዩናይትድ 1 ለ1 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 1፡30 ላይ አስቶንቪላ ከኤቨርተን እንዲሁም 4 ሠዓት ላይ በቫይታሊቲ ስታዲየም ቦርንማውዝ ከ ቼልሲ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.