Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ለነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓል (መውሊድ) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

እንኳን ለ1499ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ፡፡

በዚህ በዓል የአለሙ እዝነት መሪ፣ ለሰናዮች መልካሙን አብሳሪ፣ ለተከታዮቻቸው ሀላል እና ሀራሙን አስተማሪ የሆኑት ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምሮና መልካም ስራ የሚታወስበት፣ የሚዘክሩብትና የሚወደሱበት ነው፡፡

ይሄን በዓል በጋራ ስናከብር በፍቅር አብረን እየኖርን፣ በጋራ ለትውልድ የምትሆን ሀገርን እየገነባን፣ እንደተለመደው የመርዳዳት ባህላችን እየጠበቅን፣ አብሮ ተካፍሎ በመብላት እና ሰላማችን በመጠበቅ እንዲሁም በማፅናት ጭምር ሊሆን ይገባል፡፡

በተጨማሪም በዓሉ ሲከበር በብዝኃነት ውስጥ የሚያንፀባርቁ ዕሴቶችን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲሆን መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡”

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.