Fana: At a Speed of Life!

ሼህ አላሙዲን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሰራተኞች ላስመዘገቡት ውጤት አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞችና አመራሮች እውቅና ሰጥቷል ።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሰይድ መሃመድ÷ድርጅቱ በ2016 በጀት ዓመት የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረትም በበጀት ዓመቱ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ40 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ነው የገለጹት፡፡

በመርሐ ግብሩ ሼህ መሃመድ ሁሴን አላሙዲን በበይነ መረብ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ላስመዘገቡት አመርቁ ውጤት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም የድርጅቱን ስኬታማነት ለማጠናከር ሰራተኞች እና አመራሮች በትጋትና በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

ድርጅቱ ላገኘው ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 430 በላይ ሰራተኞች ሰርተፊኬትና ከ100 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደተበረከተላቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.