በክልሉ በ2017 ከ10 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የትምህርት ዘመን 10 ነጥብ 1 ሚሊየን ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ገለጹ፡፡
የተማሪዎች የምገባ መርሐ-ግብር የትምህርት ተሳትፎና የውጤታማነት ችግሮች መፍቻ እየሆነ መምጣቱን ገልጸው÷ ይህን ታሳቢ በማድረግ በተጠናከረ መልኩ እየተተገበረ ነው ብለዋል፡፡
በዘንድሮው ትምህርት ዘመንም በ20 ሺህ ትምህርት ቤቶች 10 ነጥብ 1 ሚሊየን የቅድመ መደበኛና 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
በትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር አገልግሎት የማይውሉ ቦታዎችን በተቀናጀ ግብርና የማልማት ስራ እንደሚከናወንም አመላክተዋል፡፡