ቻይና የጡረታ መውጫ ዕድሜን ከፍ አደረገች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የጡረታ መውጫ እድሜን ከፈረንጆቹ 1950 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍ ማድረጓ ተሰማ።
ሀገሪቱ በእድሜ የገፉ ዜጎቿ ቁጥር መጨመር እንዲሁም የጡረታ በጀት መቀነስ ለማሻሸያው ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
ቀደም ሲል ከጉልበት ጋር ለተያያዙ ስራዎች 50 ዓመት የነበረው የሴቶች የጡረታ መውጫ እድሜ ወደ 55 ዓመት ከፍ ያለ ሲሆን ከጽህፈትና ቢሮ ስራዎች ጋር የተገናኘውና 55 የነበረው የሴቶች የጡረታ መውጫ ጊዜ 58 ሆኖ ተሻሽሏል።
እንዲሁም 60 ዓመት የነበረው የወንዶች የጡረታ መውጫ ዕድሜ 63 መሆኑ ተመላክቷል።
ይህ የጡረታ መውጫ ዕድሜ ማሻሻያ ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡
በቻይና ከጠቀመጠው የእድሜ ገደብ በፊት ጡረታ መውጣት ፍጹም እንደማይቻል ዥንዋ ዘግቧል፡፡
የጡረታ እደሜ ማሻሻያው በዜጎች የጤና ሁኔታ፣ የእድሜ ጣራ፣ የህዝብ ቁጥር እና መሰል ጉዳዮች ተለዋዋጭ እንደሚሆንም ተመልክቷል፡፡