Fana: At a Speed of Life!

የክሪስቲያኖ ሮናልዶ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ቁጥር 1 ቢሊየን ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእግር ኳስ ኮከቡ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ቁጥር 1 በሊየን መድረሱ ተገለፀ፡፡

ሮናልዶ 1 ቢሊዮን ተከታይ ያገኘው በሚጠቀማቸው የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሆን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ ተከታይ ያለው የመጀመሪያው ግለሰብ ለመሆን በቅቷል።

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ተከታዮቹን ያገኘው በዋናነት በኢንስታግራም፣ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ዩቲዩብ እና የቻይና የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ከሆኑት ዌይቦ እና ኮዋይሹ ነው፡፡

የ39 ዓመቱ አጥቂ 623 ሚሊየን ያለውን እና የእድሜ ዘመን ተቀናቃኙን ሊዮኔል ሜሲ በመብለጥ ቀዳሚ መሆኑንን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከእግር ኳስ ከዋከብቱ በተጨማሪ አሜሪካዊቷ አቀንቃኝ እና ተዋናይት ሴሊና ጎሜዝ 690 ሚሊየን ተከታዮች ሲኖሯት፣ ጀስቲን ቢበር 609 ሚሊየን እንዲሁም ቴለር ስዊፍት 574 ሚሊየን ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች ናቸው፡፡

በተጨማሪም  ታወቂው የዓለም ሬስሊንግ መዝናኛ ተዋናይ ሮክ 557 ሚሊየን ተከታዮች ሲኖሩት አሜሪካዊቷ የቢዝነስ ሴት ካይል ክሪስተን 551 ሚሊየን እንዲሁም አሜሪካዊቷ አቀንቃኝ አሪያና ግራንዲ 508 ሚሊየን ተከታዮች አሏቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.