ዓለም አቀፍ የመታወቂያ ቀንን በማስመልከት የፓናል ውይይት ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024 ዓለም አቀፍ የመታወቂያ ቀንን በማስመልከት የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡
መስከረም 16 ቀን 2017 ቀን ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ የመታወቂያ ቀን በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ እና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የተወጣጡ የዲጅታል መታወቂያ ልማት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የቨርቹዋል (ዌቢናር) ፓናል ውይይትን ይካሄዳል።
በፓናል ውይይቱ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ መታወቂያ ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆሴፍ ጄ አቲክ እና በዓለም ባንክ የአይዲ4 ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያ ጁሊያ ክላርክ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የኡጋንዳ ብሔራዊ መታወቂያ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ሊቀመንበር ሚስተር ጆሴፍ ቢርቦንዋ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ጆቴወርቅ አየለ በፕሮግራሙ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
“አስተዳደር ወደ ዲጂታላይዜሽን መለወጥ” በሚል መሪ ሀሳብ በቀጥታ ስርጭት በሚካሄደው ዌቢናር የዘርፉ ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል።