Fana: At a Speed of Life!

በጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ ተረፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥረት ህይወታቸዉን ማትረፍ መቻሉ ተሰምቷል።

ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ ክስተቱ የተፈጠረ ሲሆን ፥ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጀርመን ድልድይ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ነው የጎርፍ አደጋው የደረሰው፡፡

ሆኖም በዚህ ጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥረት ህይወታቸዉን ማትረፍ መቻሉ ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ እናትና ልጅ በወንዝ ዳርቻ ካለዉ የጎመን ማሳቸዉ ዉስጥ ጎመን በመሰብሰብ ላይ ነበሩ፡፡

በዚህ ወቅትም በድንገት ደራሽ ጎርፍ ሊወስዳቸዉ የነበረ ቢሆንም በወንዝ መሀል ባለ ድንጋይ ጫፍ ላይ ሆነዉ ህይወታቸወን ማቆየት ችለዋል ብለዋል ኃላፊው።

ይሁንና የጎርፉ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ እናትና ልጁ በጎርፉ ሊወሰዱ በተቃረቡበት ሰዓት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች ደርሰዉ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸዉ የእናትና ልጅን ህይወት መታደግ መቻሎቸውን ጠቁመዋል፡፡

በአካባቢዉ ቀደም ሲል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት ያለፈበት ሲሆን ፥ በዚህ አካባቢ ከወንዙ የሚገኘዉን ዉሀ በመጠቀም የጎመንና ሌሎች ተክሎች ማሳ የሚገኝበት እንደሆም ነው ያነሱት።

በአሁኑ ወቅትም የክረምቱ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ባለማሳዎች ተክሎቹን ለመሰብሰብ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም የሚችል በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮሚሽኑ አሳስቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.