ቢሊየነሩ ጠፈርተኛ ሳይሆኑ ወደ ህዋ ላይ የተጓዙ የመጀመሪያው ግለሰብ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቢሊየነሩ ጃሬድ ኢሳክማን ጠፈርተኛ ሳይሆኑ ወደ ህዋ የተጓዙ የመጀመሪያ ግለሰብ ለመሆን መብቃታቸው ተሰምቷል፡፡
ቢሊየነሩ በዚህን ጊዜ “ወደ ምድር ስንመለስ ሁላችንም የምናስተካክለው ብዙ አለ፤ ሆኖም ግን ምድር ፍጹም ሆና ከዚህ ትታያለች” ብለዋል፡፡
ከመሬት በላይ 435 ማይሎች (700 ኪሎ ሜትር) ከኢሳክማን የአደጋ መከላከያ (ሄልሜት) ካሜራ በመገጠሙ አስደናቂ ምስሎች መታየታቸውም ነው የተዘገበው፡፡
በዚህም ከተልዕኮው መሪ የሆኑት ሳራህ ጊሊስና ቢሊየነሩ የፊታችን ቅዳሜ ወደምድር እንደሚመለሱ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡