ጥንቃቄ የሚሻው የበዓል ወቅት አመጋገብ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የበዓላት ወቅት አመጋገብ ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገበት ለጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል፡፡
የበዓላት ወቅት አመጋገብን ጥንቃቄ የተሞላበት ማድረግ እንደሚገባም ነው ባለሙያዎች የሚመክሩት፡፡
ምክንያቱም ቅባት የበዛበት ምግብ መመገብ ጨጓራን ለህመም የመዳረግ ዕድሉ ከፍተኛ ስለሚሆን ነው ይላሉ፡፡
ጥንቃቄ የጎደለው አመጋገብ ከሆነ÷ እንደ ሆድ መንፋት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጨጓራ ማቃጠል እና ሌሎች ህመሞችንም ሊያስከትል እንደሚችል ያስገነዝባሉ።
በመሆኑም በዓላትን የጤና መታወክ ሳያጋጥም ለማሳለፍ÷ የሚዘጋጀው ምግብ ንጽህናው እንዲጠበቅ እንዲሁም ምግቦች ቅባት የበዛባቸው እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
በአመጋገብ ወቅትም ቀስ በቀስ ጨጓራን በማላመድ መሆን እንዳለበት ነው የሚመክሩት፡፡
ጣፋጭ ምግቦችን እና የአልኮል መጠጦችን ከልክ በላይ ባለመውሰድ እራስን እና ቤተሰብን ከህመም መጠበቅ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል