Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ 3 የሆቴል መስተንግዶ ሠራተኞች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11ቀይ አፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 3  የሆቴል መስተንግዶ ሠራተኞች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው አንድ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ መንገድ ሲጠቀሙ የነበሩ እግረኞችን ገጭቶ ባደረሰው አደጋ ነው የተከሰተው፡፡

ሟቾቹ ሶስቱም ሴቶች ሲሆኑ÷ዕድሜያቸው ከ25-30 እንደሚገመት የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።

ሰራተኞቹ ከሥራ ፈቃድ ወስደው ቤተሰብ ለመጠየቅ ሃና ማሪያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ሰፈር ሲጓዙ እንደነበር  ባለሙያው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ከሟቾቹ ጋር አብራ ስትጓዝ የነበረች አንዲት ሴት እራሷን ስታ ሕክምና እየተከታተለች እንደምትገኝም ጠቁመዋል፡፡

በበዓል ወቅት መሰል አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እና በእርጋታ እንዲያሽከረክሩ አቶ ንጋቱ  አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.