Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር መቅደስ በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ለወለዱ እናቶች ሥጦታ አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ለወለዱ እናቶች የአዲስ ዓመት ሥጦታ አበርክተዋል፡፡

በተጨማሪም በሆስፒታሉ ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ እናቶች የአዲስ ዓመት ስጦታ በማበረከት እና በመጠየቅ  መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የአዲስ አበባ ከተማን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በተለይ የእናቶችና ሕጻናት ጤና አገልግሎትን ለማሳደግ በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸው÷ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታልም  የዚህ አካል ነው ብለዋል፡፡

ሆስፒታሉ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች የሚወለዱበት በመሆኑና አዲስ ዓመትን በሆስፒታሉ ከወለዱ እናቶች ጋር በማሳለፋቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

2017 ዓ.ም የጤና ተቋማት ለሕብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት የሚሰጡበ እንዲሆን በትኩረት እደሚሰራ መግለጻቸውንም የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሆስፒታሉ በዛሬው ዕለት የወለዱ እና በተቋሙ የሕክምና ክትትል እያደረጉ የሚገኙ እናቶች ለተደረገላቸው  የአዲስ ዓመት አብሮነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.