Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ 21ኛ የሆነውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአዲስ ዓመት በቀን 1 ሺህ ሰዎችን የሚመግበውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ አየርጤና አካባቢ መርቀን መልካም አዲስ ዓመት ብለን ምገባ አስጀምረናል ብለዋል።

ከተማችንን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ለማድረግ ከጀመርናቸው ስራዎች አንዱ በቀን አንዴ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ ወገኖቻችንን መመገብ ሲሆን 21ኛውን የምገባ ማዕከል በረከት ገበሬዋ ገንብታ አስረክባናለች ብለዋል።

በቀጣይም ሙሉ ወጪውን በመቻል 22ኛውን የምገባ ማዕከል ገንብታ ለማስረከብ ቃል መግባቷን ጠቁመው፤ ለበጎነቷ በተጠቃሚ ነዋሪዎቹ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናት እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.