Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ ዓመት ልዩ የዋዜማ ዝግጅት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 ዓ/ም አዲስ ዓመት ልዩ የዋዜማ ዝግጅት በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ-ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሐ- ግብሩ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሥራዎች እየቀረቡ እንደሆነ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.