የሲዳማ ክልል ለ1 ሺህ 549 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 549 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርገዋል።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ለሕግ ታራሚዎች የተደረገውን ይቅርታ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች 1 ሺህ 530 ወንድ እና 19 ሴቶች መሆናቸው ገልጸዋል።
የይቅርታ ተጠቃሚዎች በጥፋታቸው ተፀፅተው በማህበረሰቡ ውስጥ መልካም ሥነ-ምግባር በመላበስና ምሳሌ በመሆን ህብረሰተሰቡንና መንግስትን እንዲክሱ ርዕሰ መስተዳድሩ ማሳሰባቸውንም ጠቅሰዋል።