Fana: At a Speed of Life!

ብርሃን የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ተቀበለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው ብርሃን የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ተቀብሏል፡፡

ትምህርት ቤቱ በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤትና በድጋፍ አድራጊዎች ትብብር ተገንብቶ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መረከቡ ይታወሳል።

በአዳሪ ትምህርት ቤቱ የሚገኙ 24 ክፍሎች እያንዳንዳቸው 16 ተማሪ እንደሚያስተናግዱ የተገለጸ ሲሆን ፥ ለዓይነ ስውራን ምቹ መሰረተ ልማት ተሟልቶ በቅርቡ መመረቁ ይታወሳል።

ትምህርት ቤቱ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ 312 ተማሪዎችን ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተቀብሏል ተብሏል።

ቀደማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በትምህርት ቤቱ ተገኝተው ለተማሪዎቹ የ’እንኳን ደህና መጣችሁ’ መልዕክትን አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በአዳሪ ትምህርት ቤቱ ለሚገኙ ተማሪዎች ለንባብ የሚያግዝ ኦርካም ቴክኖሎጂን አበርክቷል።

በፍሬህይዎት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.