Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ጽጌ ዱጉማ በአሶሳ ለተደረገላት አቀባበል አመሰገነች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ በ800 ሜትር የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘችው አትሌት ጽጌ ዱጉማ በትውልድ አካባቢዋ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ለተደረገላት አባበል አመሠገነች፡፡

ትናንት ወደ አሶሳ የሄደችው አትሌት ጽጌ÷ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ለአደረጉላት አቀባበል እና ለሰጡአት ዕውቅና ምሥጋና አቅርባለች፡፡

አቀባበሉ እና ዕውቅናው በቀጣይ ለተሻለ ሥራ እንደሚያነሳሳት መግለጿን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል።

አትሌቷ ለአስመዘገበችው ውጤት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በአሶሳ ከተማ ለኢንቨስትመንት የሚውል 1 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ አበርክቶላታል፡፡

በተጨማሪም ለአትሌቷ እና ለአሰልጣኟ የወርቅ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.