Fana: At a Speed of Life!

በፓራሊምፒክ ውድድሮች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡

በፓሪስ በተካሄደው 17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያ በ2 የወርቅና 1 የብር ሜዳሊያዎች 44ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን አስታውሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዘንድሮው ፓራሊምፒክ የተገኘው የሜዳሊያ ብዛትም በ16ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች ከተገኘው አንድ የወርቅ ሜዳሊያ የተሻለ ሆኖ ተመዝግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.