እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ከኢትዮጵያጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጻለች፡፡
በውጪ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ በተዘጋጀው ውይይት ላይ አዲስ የተሾሙት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደርና የፖርላማ ልዑካን ተሳትፈዋል።
በውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ የታሪክ፣ የባህልና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ለማሳደግ ፍላጎት መኖሩ ተገልጿል።
እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የማሳደግና በድህነት ቅነሳ ላይ በትብብር የመሥራት ፍላጎት እንዳላት የልዑካን ቡድኑ አባላት አስረድተዋል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር በግብርና፣ በትምህርት፣ በሕክምናና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ድጋፍ እንደምትሻ መናገራቸውን የም/ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡