Fana: At a Speed of Life!

 የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እና የውጤት መግለጫ አድራሻ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እና የውጤት መግለጫ አድራሻ ይፋ ሆኗል፡፡

የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን በሚከተሉት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የውጤት መግለጫ አማራጮች ከጳጉሜ 4 ቀን ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ ተመላክቷል፡፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

  1. በፖርታል፡- https://result.eaes.et

 

  1. በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- https://t.me/EAESbot

 

  1. በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡- 6284 ላይ ‘R’ን በማስቀደም የመለያ ቁጥር በማስገባት (ምሳሌ R1234567) መልዕክት በመላክ ውጤትዎን ማወቅ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

በ3ኛው አማራጭ ኢትዮ ቴሌኮም የሚያስከፍለው መደበኛ የኤስ ኤም ኤስ ክፍያ እንደሚኖር ተጠቅሷል፡፡

ከውጤት መግለጫ ፖርታልና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድና ማታም እንደሚቻልም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.