ለጋራ ብልጽግና አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ አንድነታችንን በማጠናከር መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን ተናገሩ።
የኅብር ቀን “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሐሳብ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኦሮሞ ባህል ማዕከል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
አፈ-ጉባዔዋ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ አንድነታችንን የበለጠ በማጠናከር ሀራችንን በጋራ ልንጠብቃት ይገባል።
ልዩነታችንን በማጥበብ አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገን በመሥራት የሀገሪቱን መጻኢ ጊዜ የተሻለ እንድርግ ሲሉም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት እንዲረጋገጥ እና ወንድማማችነት የበለጠ እንዲጠናከር እየሠራ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡