የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛው ውጤት በትግራይ ክልል ተመዘገበ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛው ውጤት በትግራይ ክልል መመዝገቡን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ብርሐኑ ነጋ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ÷ በዘንድሮው ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛው ውጤት 675 ሆኖ መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ከ700ው 675 ከፍተኛ ውጤት በትግራይ ክልል ቃላሚኖ ትምህርት ቤት መመዝገቡን ነው የገለጹት፡፡
ከ600ው በተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ 575 በአዲስአበባ አክሲሊየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት መመዝገቡን አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል በማህበራዊ ሳይንስ ከፍተኛው ውጤት 538 በኢትዮ ፓረንትስ ትምህርት ቤት መመዝገቡን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች 1 ሺህ 221 ሲሆኑ÷ከእነዚህ ውስጥም ከማህበራዊ ሳይንስ 45 እና ከተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ 1 ሺህ 176 ተማሪዎች እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡
በየሻምበል ምህረት እና መሳፍንት እያዩ