Fana: At a Speed of Life!

በዶሃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ “የኅብር ቀን” ተከበረ

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 4 የኅብር ቀን “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሃሳብ ኳታር ዶሃ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ ተከብሯል።

በዓሉ የኢትዮጵያውያንን ብዝሀ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ እምነትና ማኅበራዊ መስተጋብር በሚያንጸበርቅ መልኩ መከበሩም ተገልጿል።

እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊ ማንነታችን ውበታችን እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ደግሞ ለሰላማችን መሰረት መሆኑን በማሰብ ተከብሯል መባሉት ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በስነ ስርዓቱ ዲፕሎማቶች፣ የኤምባሲው ሰራተኞች እና ኢትዮጵያውያን መታደማቸውም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.