Fana: At a Speed of Life!

በናይጄሪያ የነዳጅ ጫኝ ቦቴ ባጋጠመው ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጀሪያ ሰሜን ማዕከላዊ ኒጀር ግዛት ነዳጅ ጫኝ ቦቴ እንስሳትን ከጫነ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ።

አደጋው በሰው ህይወት ላይ ካደረሰው ጉዳት ባለፈ በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።

በአደጋው በአካባቢው የነበሩ ሌሎች ተሽከርካሪዎችም በእሳት መውደማቸውን የናይጀሪያ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኤጀንሲ ዳይሬክተር አብዱላሂ ባባ አረብ ተናግረዋል።

በተሽከርካሪዎቹ ላይ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች የቀብር ስነ-ስርዓት መከናወኑን ገልጸዋል።

የግዛቱ አስተዳደር ሞሀመድ ባጎ በበኩላቸው፤ በአካባቢው ያለው መንገድ የተበላሸ መሆን የአደጋው መንስዔ ስለመሆኑ ጠቁመው፤ መሰል አደጋዎች በተደጋጋሚ እንደሚደርሱም አመልክተዋል።

በናይጀሪያ በፈረንጆቹ 2020 ብቻ 1 ሺህ 531 የነዳጅ ቦቴዎች ተጋጭተው 535 ሰዎች ሲሞቱ 1 ሺህ 142 ደግሞ ለጉዳት ተዳረገዋል ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.