Fana: At a Speed of Life!

የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በሕብር በመቆም ለተሻለ ሥራ ልንዘጋጀ ይገባል – ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በሕብር በመቆም አንድነታችንን አጠናክረን ለተሻለ ሥራ ልንዘጋጅ ይገባል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ያለውን “የሕብር ቀን” አክብሯል፡፡

በዚህ ወቅት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፥ 2016 ዓ.ም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት ዓመት ነው፡፡

ይህ ውጤት የተገኘው ሁሉም ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ኃፊነት በመወጣታቸው መሆኑንም ነው ያነሱት ፡፡

እንደ ተቋም ደግሞ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች በአግባቡ በመምራትና ዜጎች ትክክለኛ መረጃ እንዲደርሳቸው በማድረግ፣ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማጋለጥ፣ የኮሙኒኬሽን መዋቅሩ የተናበበ ሥራዎች እንዲሰራ በመቻሉ እንደሆነም አንስተዋል ሚኒስትሩ፡፡

በዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ አዲስ የዓለም አቀፍ ተቋም አባል የሆነችበት ዓመት መሆኑን አስታውሰው፥ በኢንዱስትሪ ረገድ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ያረጋገጠው ውጤት መገኘቱን፣ በምግብ ራስን በመቻልም የዓለም የምግብ ፕሮግራም ማረጋገጫ የተሰጠባቸው ውጤዎች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡

እንደ ሀገር ከ500 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ማምረት መቻሉን አንስተው፥ በሌማት ቱርፋት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በማኑፋክቸሪንግ የተገኙት ስኬቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው በሕብር መቆምና ለጋራ ስኬት መሥራት እደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ቀጣዩ ዓመት የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በሕብር በመቆም አንድነታችንን አጠናክረን ለተሻለ ሥራ ልንዘጋጀ ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ አሁን ከምንጊዜውም በተሻለ ሁኔታ ሰላሟ እየተረጋገጠ በመሆኑ ለተሻለ ስኬት እንሰራለን ብለዋል፡፡

በዚሁ የሕብር ቀን ዝግጅት ላይ ለ32 የተቋሙ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት እንደተደረገ ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.