Fana: At a Speed of Life!

የህብር ቀን በጋምቤላ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሐሳብ ጳጉሜ 4 የህብር ቀን በጋምቤላ በጎዳና ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴና በሌሎች ሁነቶች እየተከበረ ነው።

ስፖርት ለጤናና ለአካላዊ ብቃት ካለው ፋይዳ ባለፈ የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር ረገድ የጎላ ፋይዳ እንዳለው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገልጸዋል።

ወ/ሮ ዓለሚቱ ዕለቱን አስመልክተው እንደገለጹት ስፖርት ለጤናና የዳበረ አካላዊ ብቃትን ለመገንባት ካለው ፋይዳ ባለፈ የህዝቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት፣ አንድነትና ሰላም የማጠናከር ሚናው የጎላ ነው።

ስፖርት በተለይም ስኳር፣ የደም ግፊትና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም የክልሉ ህዝብ የስፖርት እንቅስቃሴን በማዘውተርና ህብረ ብሔራዊ አንድነቱን በማጠናከር የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።

“የኅብር ቀን” በሚል ዕለቱ እየተከበረ ያለው በህዝቦች መካከል ያለውን የአብሮነትና የአንድነት እሴት ይበልጥ ለማጠናከር በማሰብ መሆኑን ርዕስ መስተዳደሯ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.