ጳጉሜን 3 – የሉዓላዊነት ቀን በተለያዩ ክልሎች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 3 – የሉዓላዊነት ቀን በሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተከበረ ነው፡፡
ቀኑ “ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በተመሳሳይ በሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሉዓላዊነት ቀን በፓናል ውይይትና በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡
ቀኑ በለውጡ ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የተገዳደሩ ፈተናዎችን በመቋቋም የሀገርን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማፅናት የተሰሩ ሥራዎችን በማሰብ እየተከበረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡