Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በደምና አጥንት የፀናችና ከአባቶች የተረከብ ናት ሉዓላዊነት ሀገር ናት – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት በደምና በአጥንት የፀናች እና ከአባቶች የተረከብ ናት ሉዓላዊነት ሀገር ናት ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “ዛሬ ጷጉሜ 3 በሉዓላዊነት ቀን “ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ” በሚል መሪ ሃሳብ በለሊት ተነስቶ በነቂስ ከወጣው ከከተማችን ነዋሪ እና የፀጥታ ሃይላችን ጋር በመስቀል አደባባይ በድምቀት አክብረናል ብለዋል፡፡”

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት በደም በአጥንት የፀናች እና ከአባቶች የተረከብ ናት ሉዓላዊነት ሀገር ናት ሲሉም አውስተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ለሀገራችን የደም መሥዋዕትነት ከፍለን ያስገኘነውን ሉዓላዊነት ፤ላባችንን አፍስሰን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ለማስከበር ዛሬም ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡

ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ በሀሳብ መግባባት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሃላፊነት ስሜትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

እንደሀገር ነጻነታችንን የሚፈታተኑ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን በመከታተልና በማምከን ሒደት ውስጥ የእያንዳንዳችንን የነቃ ተሳትፎ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የሀገሪቱ የፀጥታ ሃይሎች በፈተናዎች ሁሉ አልፈው ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊት ለሚያደርጉት ተጋድሎ እና ጥረት ኢትዮጵያ ሁሌም ታመሰግናችኋለች ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በድሬዳዋ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የሉዓላዊነት ቀን ላይ ከንቲባ ከድር ጁሀር ባደረጉት ንግግር÷ እስከ ሙሉ ነፃነቷ የተቀበልናትን ሀገር በላቀና በተሟላ ነፃነቷ ለመጪው ትውልድ ለማውረስ ያለመሰሰት እንሠራለን ብለዋል፡፡

በዓሉን አስመልክቶም ለሀገር ክብር መስዋዕትነት የከፈሉ አካላትን የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ መከፈቱን የድሬዳዋ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.