Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በአቪዬሽን ሳይንስና ኤሮ ስፔስ ኢንጂነሪንግ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሊያሰለጥን ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ በአቪዬሽን ሳይንስና ኤሮ ስፔስ ኢንጂነሪንግ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሊያሰለጥን መሆኑ ተገለጸ።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት የአቪዬሽን ሳይንስና ኤሮ ስፔስ ኢንጂነሪንግ ትምህርት ቤት አስመርቆ ከፍቷል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባ ፊጣ ትምህርት ቤቱ በአየር በረራ፣ በአቪዬሽን ማኔጅመንት፣ በኤር ትራፍኪንግና በሌሎች የትምህርት አይነቶች ዝግጅት በማድረጉ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምር ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ በበኩላቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ በአቪዬሽን ዘርፍ የተያዙ ትልሞችን ለማሳካት ትምህርት ቤቱ ጉልህ አስተዋፆ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዘርፉ ያለውን የሰው ሃይል ፍላጎት ለማሟላት እንደሚረዳና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልፀዋል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽንና አየር ሃይል በአቪዬሽን ሳይንስና በኤሮ ስፔስ ኢንጂነሪንግ አብሮ ለመስራት ስምምነት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በሙክታር ጣሐ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.