ኢትዮ ቴሌኮም በ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላዊ ሰሜን ሪጂን 3 ነጥብ 5ሚሊየን ብር በሚሆን ወጪ በ61 ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 3 ሺህ 690 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የሬጂኑ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አንተነህ ፋንታሁነኝ እንዳሉት÷ በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርና በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ስር ባሉ 61 ትምህርት ቤቶች 3 ሺህ 690 ለሚሆኑ ተማሪዎች በ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል ።
ኢትዮ ቴሌኮም በትምህርት ዘርፍ ዲጅታል ቤተ-መፅሃፍት እየገነባ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ በሪጅኑ ስርም ሦስት ቤተ-መፅሃፍት ገንብቶ ማስረከቡን ገልፀዋል ።
በ2016 ዓ.ም ኢትዮ ቴሌኮም እንደሀገር በተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በስፋት እየተሳተፈ መሆኑንና ለዚህም ከ649 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ በመርሃ ግብሩ ተጠቅሷል ።
በአበበ የሸዋልዑል