Fana: At a Speed of Life!

በለውጥ ዓመታት ከተደረጉት ሪፎርም አንዱ የተቋማት ሪፎርም ነው

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት” በሚል መሪ ሃሳብ ጳጉሜን 2 የሪፎርም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡

እንደ ሀገር ያጋጠሙ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያው ስብራቶችን ለመጠገንና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ባጠረ ጊዜ ለማረጋገጥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች ተጀምሯል፡፡

በለውጥ ዓመታት ከተደረጉት የተቋማት ሪፎርም አንዱ የዴሞክራሲ ተቋማት ሪፎርም ነው፡፡

በቀደመው ሥርዓት የዴሞክራሲ ተቋማት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች ከማስከበር ይልቅ የአንድን ቡድን ጠባብ ፍላጎት ለመጠበቅ የተደራጁ የይስሙላ ተቋማት ነበሩ፡፡

በመሆኑም የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ በመመለስና ዘላቂ ሰላም በማስፈን ያጋጠመን የፖለቲካ ስብትን ለማረም እንደ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ የሕዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም፣ ፍርድ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ሪፎርም ተደርጓል፡፡

ምንም እንኳን የነፃነትና ገለልተኝነት አረዳድና ልምምድ ገና ቢሆንም ተቋማቱ ከመንግስት ጫና ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆነው ሥራቸውን ማከናወን ጀምሯል፡፡

በተጨማሪም ለዘመናት የፖለቲካ ሥርዓት ጠባቂና የአንድ ቡድን ፍላጎት አስከባሪ ተደርጎ የተዋቀሩ የፀጥታ ተቋማት ከፖለቲካ ነፃ ሆነው እንዲደራጁ፣ የሀገርና የሕዝብ ደህንነት ጠባቂ እንዲሆኑ የሕግ፣ የፖሊሲና የአደረጃጀት ሪፎርም ተደርጓል፡፡

በዚህም አስተማማኝና ጠንካራ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን መከታ የሆኑ የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት እንዲሁም የመረጃና ደህንነት ተቋማት ተገንብተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.