Fana: At a Speed of Life!

ጳጉሜን 2 የሪፎርም ቀን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት” በሚል መሪ ሃሳብ ጳጉሜን 2 የሪፎርም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡

እንደ ሀገር ያጋጠሙ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያው ስብራቶችን ለመጠገንና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ባጠረ ጊዜ ለማረጋገጥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች ተጀምሯል፡፡

ከዚህም አንዱ መንግሥት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሀገር-በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሪፎርም ቀርፆ ሲተገብር ቆይቷል፤በዚህም ሀገርን የታደገ ውጤት ተገኝቷል፡፡

እየተገባደደ ባለው ዓመት መጨረሻም የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም አካል የሆነው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

የፖሊሲ ማሻሻያው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ስብራት በመጠገን በሂደት የኑሮ ውድነትና የእዳ ጫናን ለመቀነስ፣ የክፍያ ሚዛን መዛባት ችግሮችን ለመፍታት፣ የበጀት ጉድለትን ለማስተካከልና ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል ዓይነተኛ መፍትሔ ይሆናል፡፡

የኢኮኖሚ ማሻሻያው እንዲሳካ የሀገር ውስጥ ገቢና ቁጠባን ማሳደግ፣ ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.