Fana: At a Speed of Life!

ሀገርን በትክክለኛው መንገድ ላይ ለማራመድ ውጤታማ ሪፎርሞች ያስፈልጉናል-ም/ጠ/ ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገርን በትክክለኛው መንገድ ላይ ለማራመድ ተከታታይና ውጤታማ ሪፎርሞች ያስፈልጉናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን የሪፎርም ቀንን ምክንያት በማድረግ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ÷ በለውጡ ዘመን የተለያዩ ሪፎርሞችን አሳክተናል ብለዋል።

የጸጥታ ተቋማት፣ የፍትሕ ዘርፍ፣ የግብርና፣ የአምራች ዘርፍ፣ የትምህርት ፣ የሲቪል ሰርቪስ፣ የዲጂታል ዘርፍ፣ የውጭ ግንኙነትና የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች ደግሞ በትግበራ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብልጽግና የእነዚህ ድምር ውጤት መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.