Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከቻይና መንግስት የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) -የቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የ Great Wall Commemorative Gold Medal Award አበረከተ፡፡

የተበረከተላቸው የወርቅ ሜዳሊያ የሁለቱን ሀገራት ፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ላበረከቱት ሚና እንዲሁም አሁን ላይ የዓለም አቀፍ የሕዝብ ደኅንነት ትብብር ፎረም የቦርድ አባል ሆነው ለዜጎች ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ እየተጫወቱ ላሉት ክፍተኛ አስተዋዕፆ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የወርቅ ሜዳሊያ በቻይናው የህዝብ ደኅንነት ሚኒስትር ዋንግ ዣዎሆንግ እንደተበረከተላቸው ታውቋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ፣ የቻይና የህዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትሮችና እና የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.